መነሻ ስለ መጀመሪያ የጽሁፍ ምድቦች መሰረታዊ ኮምፕዩተር ሀሁ - Learn Fidel መሆን የተካነ ባህሪ ያስተሳሰብ ጀግና

ክፍል ፫) ኦፐሬቲንግ ሲስተም ማለት ምን ማለት ነው?

mejemeriya computer Ethiopia Amharic Tatariw Addis Ababa Fantaw Tesema ለምሳሌ ኮምፕዩተር ሲቀሰቀስ የሚያቃስተውና ጊዜ የሚወስድበት መጀመሪያ ማጣራት ያለብት ስራ ስላለው ነው፡፡ የውጭና የውስጥ ሃርድዌሮቹ መስማማታቸውንና መስራታቸውን ማወቅና መቆጣጠር ስላለበት ነው፡፡ ካወቀና ከተቆጣጠረ በኋላ አንገብጋቢ ስህተት ከተገኘ ኮምፕዩተሩ መልእክት ያሳያል ወይም ይቆማል፡፡ ኮምፕዩተሩ ከጀመረ በኋላም ኦፐሬቲንግ ሲስተሙ በዚሁ ተግባር ይቀጥላል፡፡ ከኦፕሬቲንግ ሲስተም ውጪ ሃርድዌርና ነጠላ ሶፍትዌር ብቻቸውን ምንም አያፈይዱም፡፡

ፕሬቲንግ ሲስተም፤ በኮምፕዩተር ተግባር እይታ የሁሉም ትእዛዝ ጥርቅሞች አስተዳዳሪና ተቆጣጣሪ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዊንዶውስ፣ ማክ እና ሊነክስ ዋና ዋና የሚባሉት ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ናቸው፡፡ ዊንዶውስና ማክ በገንዘብ የሚገዙ ናቸው፡፡ ሊነክስ ግን ነጻ ነው፡፡ የነጻ ምንጭ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይባላል፡፡ ሊነክስ በመቶ የሚቆጠሩ ዝርያወች አሉት፡፡

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!

አስተያየት መስጫ፤

* ተፈላጊ መረጃ
1000
Captcha Image

አስተያየቶች

እስከ አሁን አስተያየት አልተሰጠም፡፡ የመጀመሪያ ይሁኑ!