መተዋወቅ ክፍል ፩ መተዋወቅ ክፍል ፪

በሃሳብ ተጠያይቆ መተዋወቅ! ክፍል ፩፤

August 7, 2004. እርማት 2020

ዳመጥና መጠየቅ ህይወታችን ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ለምሳሌ ሁላችንም በሚባል ደረጃ ስንደመጥ ደስ ይለናል፡፡

በሃሳብ ተጠያይቆ መተዋወቅ! ክፍል ፩፤

mejemeriya computer Ethiopia Amharic Tatariw Addis Ababa Fantaw Tesema ኛን ፍላጎት ለመረዳት ሰው ዝግጁ ሆኖ ቀርቦ ፍላጎት ሲያሳይ ዋጋ እንሰጠዋለን፡፡ የደስታችን ተካፋይ ስናገኝ ያስደስተናል፡፡ የሃዘናችን ተካፋይ ስናገኝ ወዳጅ ከጎናችን እንደቆመ ሆኖ ይሰማናል፡፡ በተቸገርን ጊዜ የሚረዳን ሰው ስናገኝ ውለታ እንዲንመልስ ፍላጎት ያሳድርብናል፡፡ እንደምታዩት የሰው ልጅ በስጋ ብቻ ሳይሆን በፍላጎትና በስሜት ጭምር ዝምድና አለው፡፡ በመጠየቅ ዙሪያም ቢሆን በትክክል ከጠተቀምንበት ብዙ እንመሳሰላለን፡፡ ለምሳሌ ስለኛ ስንጠየቅ ሰወች እኛን ለማወቅ ፍላጎት እንዳለቸው እናውቃለን፡፡ ወይም አናውቅም፡፡ ወይም አናውቅም ያልሁበት ምክንያት ብዙ ኢትዮጵያውያን ከሰላምታ ውጭ ብዙ መጠያየቅና መተዋወቅ ላይ ያለን ፍላጎት አነስተኛ ስለሆነ ነው፡፡

mejemeriya computer Ethiopia Amharic Tatariw Addis Ababa Fantaw Tesema ወች አንዳንድ መደበኛ ጥያቄ ተጠይቀው ከመለሱ በኋላ አንተስ/አንችስ ብሎ መጠየቅ የተለመደ አይደለም፡፡ መደበኛ ጥያቄወች ማለት ለምሳሌ፤ ምን ትሰራለህ፣ የት ትኖራለህ፣ ምን ትወዳለህ፣ ዛሬ ቁርስ ምን በላህ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አሁን ተጠየቂው ምን እንደሚሰራ፣ የት እንደሚኖር፣ ምን እንደሚወድ፣ ቁርስ ምን እንደበላ ባጭሩ ይመልሳል፡፡ በኋላ ግን አንተስ/አንቺስ ብሎ የሚጠይቅ በጣም ጥቂት ነው፡፡ የአንድ አቅጣጫ ጥያቄ ብቻ ሆነ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ጠያቂው ተመሳሳይ ጥያቄ ቢጠየቅ አይከፋውም፡፡ ጠያቂው ሳይጠየቅ፤ በራሱ ተነሳሽነት እኔ ደግሞ ይኸን እሰራለሁ፣ እዚያ እኖራለሁ፣ ይኸን እወዳለሁ፣ ቁርሴን በልቻለሁ እያለ ሳይጠየቅ ከዘላበደ ይደብራል፡፡ ወይም ሁኔታውን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ነገሩን ያነሳሁት መጠየቅ ለማፋጠጥ ሳይሆን ለመተዋወቅ ምርጥ ከሚባሉት አጋጣሚወች አንዱ ነው፡፡ ሰው ተጠይቆ ካልጠየቀ መተዋወቅ ከባድ ነው፡፡ ተጠያቂው ስለተጠየቀው ብቻ ተናግሮ ሌላ ያተረፈው ነገር የለም፡፡ ጠያቂው ደግሞ መልስ ብቻ አግኝቶ ስለሱ ሳይናገር ብዙ ያተረፈው ነገር የለም፡፡ ይኸ ፈጠራ አይደለም፡፡ በተለያዩ አጋጣሚወች ላይ እኔ ልብ ብያለሁ፡፡ ሰወችን ለማወቅ ልባዊ ፍላጎት ባሳይም እነሱ አይጠይቁም፡፡ እኔ ይኸን እንደ ክፋት ሳይሆን እንደ ልምድ ማነስ እወስደዋለሁ፡፡

mejemeriya computer Ethiopia Amharic Tatariw Addis Ababa Fantaw Tesema ኔታው ወደ ቁምነገር ከፍ ሲል ደግሞ በጣም ይብሳል፡፡ ለምሳሌ የእናንተ ባህልና ቁንቋ ምን ይመስላል ብሎ የሚጠይቅ ጥቂት ነው፡፡ ምክንያቱም ጠይቆ ለማወቅ ያለን ፍላጎት ለበጎ አላማና ልምምድ በቂ መሰረት እንዲኖረው በደንብ ስላልተሰራበት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ይገርመኛል፡፡ በቀላሉ መለማመድ የምንችለው ነገር ለመቀራረብና ለመተዋወቅ ያስችለን ነበር፡፡ መተዋወቅ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በህብረሰብና በሃገር ደረጃም ትልቅ ሚና አለው፡፡ ለመተዋወቅና ለማወቅ ፈቃደኛ የሆነ ህብረተሰብ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሃገሩንና ታሪኩንም ጭምር ሳያዛባ ያውቃል፡፡

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!

አስተያየት መስጫ፤

* ተፈላጊ መረጃ
1000
Captcha Image

አስተያየቶች (1)

Gravatar
አዲስ
አመለ(Norway)እንዳሉት...

ጥሩ እይታ ነው ፈንታው:: እናመሰግናለን????????????

በጽሞና ማዳመጥ ወይም መደማመጥ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደርጃ ለመግባባትና ለመተዋወቅ ወሳኝ ነው:: እዚህ ሀገር አብዛኛው የእኛ ሰው ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣን ጥያቄ ደስ ብሎን ነጻ ሆኖን ለመመለስ ስንቸገር ይታያል:: ፍላጎትም አይታይብንም ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ልንሰጥ እንችላለን::

በተጨማሪም እኛ ከሌላ ሀገር ሰዎች የሚመጡ የግል የታሪክ የባህል የሀይማኖት ወዘተ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከቋንቋ በተጨማሪ የእውቀትና የዝግጅት ማነስ ስላለብን እንዲሁም መጠራጠር ስለምናበዛ ከመጠየቅም ከመጠየቅም ስንቆጠብ ይስተዋላል:: በዚህም ምክንያት እኛም ስለሌላው በደንብ እንዳናውቅ ወይም ጥራዝ ነጠቅ ትንሽ እውቀት ብቻ እንዲኖረን ሲያደርግ ስለእኛም ለሌሎች በሚገባ ሳናሳውቅ ይቀራል::

አስተዳዳሪ:

ለትውውቅና የተለያዩ ነገሮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረን የጠቀሻቸው ምክንያቶች እንዳይከለክሉን ሁላችንም የተሻለ ማድረግ እንችል ነበር፡፡ ለአስተያየትሽ አመሰግናለሁ አመለ! መልካም ውሎ!
ፋንታው