You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ቤት ወይም ቢሮ ውስጥ የስራና የመዝናኛ መብራት መጠን! ለአይንዎ ያስቡለት!!

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 04/10/2015 - 12:13
Tatariw Ethiopia Amharic addis ababa Ethiopian flag wake up

ሁኑ ዘመን ቤት ውስጥ ቴሌቪዢን ወይም የአስሊ መታያ ፊት ተቀምጠን ብዙ ጊዜ እናሳልፋለን። ይህን ስናደርግ የአካባቢው መብራት መጠን ደብዛዛ ወይም ጨለማ ከሆነ ለአይናችን አስቸጋሪ ስራ መስጠት ነው። የቴሌቪዢንና የአስሊ መታያ ፊት ብርሃን ይበዛበታል። አይናችን የአካባቢውን ጨለማ አቋርጦ ለማየት ሃይል ይጠቀማል። ሌላው ደግሞ አይናችን ከአካባቢው ጨለማ በኋላ የመታያው ብርሃን ላይ ሲያርፍ እንደገና ሌላ አይነት ሃይል ይጠቀማል። ለምሳሌ ፊልም ወይም እግር ኳስ ቤት ውስጥ በምናይ ጊዜ የአካባቢው መብራት መጠን ከመታያው መብራት መጠን በጣም ያነሰ ነው። በተለይ በተከታታይና ለረጅም ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታወች ሲደጋገሙ አይኖቻችን በተመሳሳይ ጊዜና በየሰኮንዱ ከጨለማና ከብርሃን ጋር ለመመሳሰል የሚጠቀሙት ሃይል አይን ላይ ድካም ይፈጥራል። የአካልም ድካም ሊፈጥር ይችላል።

ሮ ውስጥ ሲሆን ግን ብዙ መስሪያ ቤቶች የቢሮውን መብራት ተመጣጣኝ ለማድረግ ይሞክራሉ። የቢሮ ስራ በአብዣኛው ቀን ላይ ስለሆነና የውጭ ብርሃን ወደ ውስጥ ስለሚገባ መብራት ለማስተካከል ይቀላል። ሌላ ቦታ ደግሞ እንደሚታወቀው ፊልም ቤቶች ጨለማወች ናቸው። ይህ የቆየ አሮጌ ግን ጥሩ ባህል ቢሆንም ምክንያት አለው። ፊልም ቤት ፊልም የሚያሳየው ማሽን የአካባቢው ብርሃን ጨለማ ካልሆነ ፊልሙ በደንብ አይታይም። ማሳያ ማሽኖች አሁን የተሻሻሉ ቢሆንም ባህሉ ግን ያው ነው። ለማንኛውም ሰው ወደ ፊልም ቤት በየቀኑ ስለማይሄድ ጉዳት የለውም።

ካባቢው መብራት መጠንና የመታያው መብራት መጠን ሲመሳሰል አይን ይዝናናል። ጨለማ፣ መብራት፣ መብራትና ጨለማ እያለ ስለማይጨነቅ አይን ደስ ይለዋል። ሰውም በራሱ ጥሩ ይሰማዋል። ሰውነቱን አይጫጫነውም። አይኑን ብዥ አይልበትም። በቂ መብራት ሲኖር ንቃትም ይሰጣል። ክፍል ውስጥ በቂ መብራት በሚኖር ጊዜ ሰው በራሱ ቴሌቪዥኑን አጥፍቶ ለማንበብ እራሱን ሊጋብዝ ይችላል። ስንፍናም ይቀንሳል። ክፍል ውስጥ በቂ የመብራት መጠን በማግኘት ብቻ ሰው ለመብራት ብዙ አይከፍልም። ከመብራት ዋጋ ይልቅ ሰው ለአይኑ ቢያስብ የተሻለ ነው። በነገራችን ላይ ቴሌቪዢን ሲያዩ መብራት ማጨለም/ማጥፋት መጥፎ ልምድ ነው። በቂ መብራት ማግኘት ለአይን ብቻ ሳይሆን ከላይ እንደጠቀስኩት ሌሎችም ጥቅሞች አሉት። እንዳውም አንዳንድ ሰወች በቂ መብራት እንዲኖራቸው ከተለማመዱ የማንበቢያ መነጸር አያስፈልጋቸውም ይሆናል። አይነወን ላለማስቸገር ከፈለጉ፤ የትም ቦታ ቢሆን፤ በተለይ ለማንበብ በጣም በቂ የሆነ መብራት መጠን ያስፈልጋል። አስሊ ላይም የሚሰሩ ከሆነ መብራትን በተመለከተ ልክ እንደ ቴሌቪዡኑ ቢሆንም መታያ ላይ ቀርበው ነው የሚያዩት። ስለዚህ ለምሳሌ በየ ሰአቱ ትንሽ እረፍት ማድረግ ለሃሳብም ሆነ ለአይን ጥሩ ነው። አንዱ እረፍት ማድረጊያ ዘዴ በየ 30 ደቂቃወች ውስጥ ለ30 ሰኮንዶች ያህል አይንወን ሌላ ነገር ላይ ማሳረፍ ለአይንወ እረፍት መስጠት ነው። አስሊ ላይ በሚሰሩት ስራ ላይም ለማሰብ ጥሩ ነው። አይንወ ሌላ ቦታ ላይ ስላረፈ ስራ አይፈቱም!!! አይንወን የበለጠ መርዳትና መንከባከብ ከፈለጉ ደግሞ ያለወት የአስሊ መታያ ጸረ-አንጸባራቂ መሆን አለበት። ጸረ-አንጸባራቂ መታያ ልክ እንደ መስታወት መልክና ሌላ ነገር ከኋላ አንጸባርቆ አያሳይም። ምሳሌውን ለማወቅ እዚህ መመሪያ ጽሁፍ ውስጥ ከላይ የገባውን ፎቶ ይመልከቱ!!!

ደ ቤትና ቴሌቪዢኑ እንደገና ስንመጣ ደግሞ ሁልጊዜም ስለመብራት ድርቅ ማለት አያስፈልግም። ለምሳሌ ልክ እንደ ፊልም ቤቱ አንዳንድ ጊዜ መብራቱን ጨለም/ደብዘዝ አድረጎ፤ በጥሩ የሮማቲክ ፊልም ከፍቅረኛ ጋር ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎና ተቃቅፎ እያዩ መዝናናት ቆንጆ ነው።

ማጠቃለያና ዋና ነጥብ፤

  • ቴሌቪዢንና የአስሊ መታያ ፊት ሲቀመጡ አይንዎ እንዳይቸገርና ስራ እንዳይበዛበት የአካባቢው መብራት መጠን ከቴሌቪዢንና የአስሊ መታያ መብራት መጠን ጋር መመሳሰል አለበት።
  • ያለወት የአስሊ መታያ ጸረ-አንጸባራቂ መሆን አለበት። ጸረ-አንጸባራቂ መታያ ልክ እንደ መስታወት መልክና ሌላ ነገር ከኋላ አንጸባርቆ አያሳይም።
  • ወረቀት ላይ ለማንበብ ደግሞ አሁንም አይንወ እንዳይቸገርና ስራ እንዳይበዛበት የአካባቢው መብራት መጠን በተቻለ መጠን ልክ ውጭ ፀሃይ ያለችበት ጋር መመሳሰል አለበት።

በተረፈ መልካም እድል!!!

Comments

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ