You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ምግብ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ይበላል፡፡ ማሰብም መብላት ነው!

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 03/06/2015 - 20:00
tatariw ethiopia amharic addis ababa passions food Ehiopia

ህ ጽሁፍ ካለፉት ጽሁፎች እይታና አላማው የተለየ ነው። ምክንያቱም ጥራት ያለው ምግብ፣ መጠጥና አስተሳሰብ የቱን ያህል በሰው ህይወት ላይ አስተዋጾ እንደሚያደርጉ በምችለው ለማብራራት ነው። ለምሳሌ መጥፎም ይሁን ደግ በተናገርነው ነገር ሰወች ያስታውሱናል። የሰራነው ስራ ይከተለናል። ጥሩ ምሳሌ ስንሆን ሰወች ይከተሉናል። ይህ ሁሉ ከአስተሳሰብ ጋር ግንጙነት አለው። ወደ አዕምሯችን ይገባል። ልክ እንደ ምግብና መጠጥ ወደ ሰውነታችን ይገባል። ለህይወታችን ቅርጽ ይሰጠዋል። በተለይ አስተሳሰብ ማንነታችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ሌሎች ቁሳቁሶች ይልቅ ምግብ፣ መጠጥና አስተሳሰብ ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ስለሆኑ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል። ቅድሚያ ልንሰጥ የምንችለው ግን አቅማችን ከቻለ ነው። አብዛኛው ሰው የመምረጥና ቅድሚያ የመስጠት አቅም ያለው ይመስለኛል። ልብስና ጫማ ሰውነት መሸፈኛ ነው። ቤትና መኪና ህይወትን ያቀላል። እነዚህ አያስፈልጉም ማለቴ ሳይሆን ወደ ሰውነታችን የሚገቡ አይደሉም ለማለት ነው። ቅድሚያና ትኩረት መሰጠት ያለብን ወደ ውስጥ ለሚገባው እንጂ ከውጭ ለሚታየው አይደለም ለማለት ነው። ቁሳቁስም ቢሆን አቅም እስከፈቀደ ድረስ ሰው ጥሩ ነገር ቢኖረው በራሱ እርካታ ነው። የስራም ውጤት ነው። ባለቤቱ ደስ እያለው ይጠቀምበታል። ሁሉም እንደአቅሙ፣ እንደምርጫውና እንደገቢው ሚዛን አድርጎ መያዝ ይችላል።

ወደ ውስጥ የሚገባ አስተሳሰብ፤

ተፈጥሯችን ስለ ብዙ ነገር እናስባለን። ፈልገንም ሳንፈልግ ብዙ ነገር እንሰማለን። ብዙ ነገር እናያለን። የምናስበው ነገር እራሳችንን ብቻ ሳይሆን ሌላም ሦስተኛ ወገን ሊነካ ይችላል። የሰማነው ነገር ሊያበሳጨን ወይም ሊያስደስተን ይችላል። ባየነው ነገር ምክንያት ልንጠላ ወይም ልንወድ እንችላለን። እነዚህ አስተሳሰቦች ለክፉም ይሁን ለደግ ወደ ውስጣችን የምናስገባው ነው። ለክፉም ይሁን ለደግ ለሌሎች አስተላልፈን የምንሰጠው ነው።

ተቃራኒው ደግሞ አንድ ሰው ደግና አክባሪ ሆኖ ሌሎች በክፉ ሊያስቡት ይችላሉ። የሰወችን ሃሳብ መቆጣጠር አይቻልም። ነገር ግን ሃሳቡ የግለሰቡን ህይወት የሚነካ ከሆነ ዝም ማለት አያስፈልግም። መፍቀድም የለበትም። በሌሎች ምክንያት እርስዎ የሚያጡት ትንሽና ቀላል ነገር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ነገሮችንም ንቀው ሊያልፏቸው ይችላሉ። የሚያጡት ነገር ወደ ትልቅነት ሲቀየር ደግሞ ነጻነት፣ ሃገርና ሃይማኖት ሊሆን ይችላል። ከነጻነት፣ ከሃገርና ከእናት የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። እናቱ ብትሰደብበት ማንም ዝም የሚል የለም። ሃገሩንና ነጻነቱን ሲቀሙት ግን ዝም የሚል አይጠፋም። ይህ ሁሉ ከአስተሳሰብና ከአቅም ጋር ግንኙነት አለው። ከውጭ ተጽዕኖ ተደርጎ ወደ ውስጥ የሚገባ አስተሳሰብ ወይም ተጽእኖ ነው። ይህ በሚደርስ ጊዜ በራስዎ ህይወት ላይ እራስዎ መወሰን አልቻሉም ማለት ነው። ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ ጎጂ አስተሳሰብ ገና ከመድረሱ በፊት መከላከል አለብዎት። ወደ ውስጠዎም ገብቶ ከሆነ ታግለው ማስወጣት አለብዎት። በራስዎ ህይወት ላይ እራስዎ መወሰን ከፈለጉ መጥፎውን አስተሳሰብ የሚከላከል ግንብ መስራት አለብዎት። እጂ መስጠት የለም። ምክንያቱም እጂ የሰጠ ሁልጊዜ ተቀምቶና ጎድሎበት የሚኖር ብቻ ነው። ይህ ሊደርስ የሚችለው መሰረቱ ከአስተሳሰብ ጋር ግንኙነት ስላለው ነው።

በሌላ መልኩ ደግሞ እራስዎ የፈጠሩት መጥፎ አስተሳሰብ እራስዎን እንዳይጎዳዎት ልብ ማለት ያስፈልጋል። አስተሳሰብዎ ሌሎችን እንዳይጎዳ ደግሞ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ለምን ሰው ጋር ይቀያየማሉ? ከዚህ በፊት የተቀያየሙትም ሰው ካለ ሌላ ተጨማሪ ሰው ጋር መቀያየም አያስፈልግም። ብዙውን ጊዜ ሰውን ሊያራርቅ ወይም ሊያቀራርብ የሚችለው አስተሳሰብ ነው።

ባጠቃላይ ወደ ውስጣችን የሚገባው ምግብና መጠጥ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ጭምር ስለሆነ ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ማሰብም መብላት ነው!

main category:

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ