You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

እራቁቱን የነበረው ግድግዳ፤ ስዕል እስከሚያገኝ ታሪኩ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Wed, 10/16/2013 - 21:30
first image: 

ራቁቱን የሆነው ግድግዳ
ስዕል አጥቶና ሰንብቶ
ልገዛለት ሳስብ ሳይሳካ ቀሮቶ
ብዙ አምት አልፎ፡፡
ድንገት በመንገድ ላይ አንድ ቀን
የሚሸጥ አየሁኝ መንገድ ላይ ተዘርግቶ
ይቻል ነበር ዋጋም መከራከር
ደስ ያለኝን ሁለት ስዕል ገዝቼ
ለምስኪኑ ግድግዳ አንድ ጨምሬለት
ተመለስኩ ወደቤት ግድግዳውን ለማሳየት፡፡

ሁንም ሰንብቶ
ከሁለት ሳምንት በኋላ
ስዕሉ ፍሬይም ስለሚያስፈልገው
ባለ-መስታወት ፍሬይም ገዝቼለት
አስገብቼ ስሞክረው
ቀረ ሳይመቼው
እንደ መኮራመት አደረገው፡፡

የገዛሁት ስዕል ለካ የሚወጠር ነው
መስታወት የገዛሁለት ለካ ሳይገባኝ ነው!

ጉዞ ወደ ፍሬም ጥበበኛው ቤት
አሁን ሌላ ወጭ?
አቦ ግድግዳውን ደስ ይበለው!
ጥበበኛው ሱቅ ዘንድ ስደርስ
ዋጋው ውድነቱ፤ ምርጫው ብዛቱ
ካሁን በኋላ አልለፋም ከዚሁ ልግዛ
አላጣም የሚስማማ
እያልኩ ሳሰላስል ጥበበኛው ቀረበኝ
ምርጫየን ሊረዳኝ፡፡

ኩየ ቢሆንም ጥበበኛው ......
ከዚህ በፊት እንደሚያውቀኝ
በወሬ ጠመደኝ
ዋጋውን እንደመናገር ወግ አበዛብኝ፡፡

ሰወች ለጥሩ ነገር መክፈል ይፈራሉ
ለ30 ደቂቃ ታክሲ ዋጋ የአፍታ ደስታ
ስዕልህን ግን ሁል ጊዜ ታየዋለህ
ትደሰትበታለህ፤ ትረካበታለህ
እኔም የተስማማሁ መሰለኝ
አረ ይኸ ሰውዬ በወግ አዘገየኝ
ወሬውም አሳመነኝ
የፍሬሙን ዋጋ አስረሳኝ፡፡

እንደምንም ሁለቱን ስዕሎቼን ሲለካ
እንዴት ናቸው ስለው
አየት አደረገና ጥሩ ናቸው
ግን ከየት ገዛሃቸው?
ድንገት ከመንገድ ላይ!
አሃ እስከሚያባሯቸው ድረስ መንገድ ላይ የሚሸጡ አሉ፡፡

ሬሙ እስከሚያልቅ ሶስት ሳምት ይወስዳል
ሲያልቅ ይነገርሃል
እሺ በደንብ ስራው ጥራት እወዳለሁ
በዚሁ ተስማምተን ውልቅ ብዬ ወጣሁ፡፡

በኋላ ሳሰላው የፍሬሙን ዋጋ
አራት ጊዜ እጥፍ ከስዕሉ ዋጋ
ወቼው ጉድ እያልኩኝ
ለካ ለዚህ ሆኗል በወግ የጠመደኝ
መቼም በጥራት የሰራዋል! ብዬ ተጽናናሁኝ፡፡

ሶስት ሳምንቱ ደርሶ
ስዕሎቹም መጥተው
ከግድግዳወቹ ላይ ወዲያው ተንጠልጥለው
እኔም በደስታ መጨረሻ ላይ ስል
የልፋቴን ዋጋ ለግድግዳው ትቼ
ጠርዞቹን ሳያቼው ትራፊና ምስማር
አሁን ትራፊና ምስማር ከውጭ ምን አወጣው?
ያ ጥበበኛ ሰው
ምን ነካው?
በጥራት ተስማምተን!

ሁን እንደገና በደጥበበኛው
ትርፍና ምስማሩን እንዲያስተካክለው
ይኸ ይስተካከል ገና ከማለቴ
እኔኮ የወጠርኩት በተስማማነው ነው
ያ ከሆነ ታዲያ ትራፊው ምንድነው?
ምስማሩስ እንደዚህ ከጎን የሚታየው?
ትራፊና ምስማር ቦታው ከውስጥ ነው!
የተስማማነውም ከጥራቱ ላይ ነው፡፡

አወ አስታውሳለሁ
ታማኝ ስለሆነ መቼም ኖርዌጂያዊ!
ከዚህ በላይ እንኳን እያጋነንክ ነው
እንደዚህ እንዳተ ደርሶብኝ አያውቅም
የቻልኩትን ሁሉ አድርጌልሃለሁ
ለሃያ አምስት አመት ይህን ሰርቻለሁ፡፡

ጥሩ ነው እንደዛ ዋጋ እሰጠዋለሁ
አሁን ግን እባክህ
ከጎን የማየውን አስተካክለው እስቲ
እዛው ግድግዳ ላይ ሰቅየ ሳሳየው
በቃ እሞክራለሁ አለኝ ጥበበኛው፡፡

ሳምንት በኋላ መልዕክት ሲደርሰኝ
ስዕሌን ላመጣ ወደ ሱቁ ሄድኩኝ፡፡፡
ሁለቱንም ስእል ከላስቲኩ አውጥቶ
አራቱንም ጎኖች እያዞረ አይቶ
ለኔም አሳይቶ፡፡
አሁንስ እረካህ? አለኝ ተኩራርቶ፡፡

ከጠበቁት በላይ በደንብ ሰለሰራው
እኔም ፐርፌክት አልኩት
ይኸን ነበር የፈለኩት
እሱንም አመሰገንኩት፡፡

ሁለቱ ስዕሎች ኮተታቸው በዝቶ
አባካኑኝ እኮ!
ሚስኪኑን ግድግዳ ደስ እንድለው ብየ
እስከመጨረሻው እሱን ለማሰደሰት
እኔም እጄን ሳልሰጥ፡፡

Comments

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ