You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ሞገደኛው ባለሎሚ በአውሮፓ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ ሲከንፍ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sun, 03/20/2011 - 19:24
first image: 

ጣቱ ፍቅረኛውን ለመቀበል በደስታ ድዱን እያሳየ አውሮፕላን ጣቢያ ከተፍ ይላል፡፡ ታዲያ ምን ይሆናል ልጅቷ ባህል ረስታ ወደ ሰማይ ማየት ጀምራለች፡፡ በአውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፍቅረኛሞች ነበሩ፡፡ ሁለት የተለያየ ሃገር ውስጥ ስለሚኖሩ አንድ ቀን ሴቷ በተራዋ ወንዱ ወደሚኖርበት ሃገር ለጉብኝት በአውሮፕላን ከተፍ ትላለች፡፡ እሱም ሊቀበላት ወደ አውሮፕላን ጣቢያው ፈገታውን ጨምሮ እየከነፈ ይሄዳል፡፡ መውጫው ላይ እሱ ሲጠብቅ እሷ ደግሞ ስትመጣ ተያዩና ልክ እንደደረሰች ምንም ፋታ እንኳን ሳይሰጣት ከኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አወጣና....

እሱ ፡ "እንቺ፡፡ ያዢ፡፡" ይላታል፡፡
እሷ ፡ የተሰጣትን አየት ታደርግና በመገረም " What the hell this is? " አለችው፡፡
እሱ ፡ ሎሚ ነዋ! አታውቂም? ባገራችን በኢትዮጵያ ባህል ለፍቅረኛ ሎሚ ይሰጣል!
እሷ ፡ የትኛው ባህል? የት?
እሱ ፡ አገርቤት ነዋ! በተለይ ገጠር አካባቢ፡፡
እሷ ፡ "እ እ እ እ እ" አለች ወደ ሰማይ እያየች፡፡ ሎሚውን በቅጡ ሳታየው ዝም ብላ በጇ እንደያዘች፡፡
እሱ ፡ አረ እባክሽ አሽቺው! ማሽተት እኮ ያስፈልጋል፡፡
እሷ ፡ ትንች ሸተት አደረገችና፣ የታችኛውን ከንፈሯን ሸፈፍ አድርጋ "እ እ እ እ እ" አለች አሁንም ወደ ሰማይ እያየች፡፡
እሱ ፡ ይቺ ልጅ ስለሎሚ አታውቅም እያለ በልቡ፣ የጃኬቷን ኮሌታ እንደሚጣላ ሰው ጭምድድ አድርጎ ይዞ ስቦ ወደሱ አስጠጋትና ግጥም አርጎ ሳማት፡፡
እሷ ፡ አፈር ፈገግ.....
እሱ ፡ አሁን በቃ ተይው፡፡ እንሂድ፡፡

ደ መኪናው ሲሄዱ እሱ በልቡ ሁኔታው እየገረመው፣ አሁን ይህንን የመሰለ ሎሚ አስቤ ገዝቼ የተረዳኝ የለም እያለ ያስባል፡፡ የሰጠኋት ሎሚ ደግሞ ትልቁ የፈረንጂ ሎሚ ሳይሆን ደንበኛው ትንሹና አይናማው ሎሚ ነው፡፡ አረንጓዴና ቢጫ ቀለም ያለው፣ ከቀይ በስተቀር የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሊመስል ምን ቀረው? ይቺን ልጅ ምን ነካት እያለ እራሱን በውስጡ እየጠየቀ መኪናዋ ጋ ደረሱ፡፡

ከዛም ቆይታዋን ጨርሳና ከርማ ተመለሰች፡፡
ያው እንደሚታወቀው ፍቅረኞች የተለያየ ሃገር ሲኖሩ የተለያየ ኮተት አለው፡፡ እና ያው እንደተለመደው በስልክ ሲጠያየቁና ሲጫወቱ ከዕለታት አንድ ቀን ግርግር ተፈጠረ፡፡ ግርግር በስልክ!

እሷ ፡ አንተ ወርቅ አግኝተህ መያዝና መወሰን አልቻልክበትም፡፡
እሱ ፡ በደንብ ጥሩ እንዲሆንልን ቀስ እንበል፡ አይዞሽ፡፡
እሷ ፡ ምን? እና እኔ መሆን አልችልም ማለት ነው?
እሱ ፡ አንቺን ማን አለሽ?
እሷ ፡ ዝም በል! አንተ ዝም ብለህ ጊዜየን ታቃጥላለህ፡፡ እንዳውም እኔ እኮ የጨዋ ልጅ፣ ቆንጆና የተማርኩ ነኝ፡፡ እበዛብሃለሁ፡፡ አንተ ላበሻ ሴት አትሆንም፡፡ ፈረንጅ አግባ፣ እሺ! ባላገር!!
እሱ ፡ "ዝም፡፡" ( ስለ ሎሚ የማታውቅ አበሻ ልጅ፣ እሱን ላበሻ ሴት አትሆንም ስትለው በልቡ እየገረመው፡፡

Comments

Goradaw

I love to read this intersting script. I am higly impressed how the guy loves his tradition. We ethiopian lose our identity , we are always looking for the modern values of the whites. We do undermine our customs. We label the people who respect our innocent and beautiful cultures as BALAGER. It gives me invaluable lessons Tatariw.I think we are trapped by Identity crisis even if we now and then claim that we are proud Ethiopians and we have 3000 years history. It is totally empty and senseless if we don't practice it and take it to the ground, God bless you . Forsett å skive denne slags historier….Goradaw

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ