You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የከረመ ብርጭቆና የግር ኳስ ጨዋታ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 10/28/2011 - 21:08
first image: 

ጅቷ ከትምህርት በኋላ አንዳንድ ጊዜና በተለይ ቅዳሜና እሁድ ወደሱ ጋ ለጉብኝት ትመጣለች፡፡ ምግብ ባንድ ላይ እየተጫወቱ ከበሉ በኋላ ተይው ቢላትም አይሆንም እያለች ብርጭቆና ሳህን ሳታጥብ አርፋ መቀመጥ አይሆንላትም፡፡ ምግብ ከተበላ በኋላ እቃዎቹ መታጠብ አለባቸው ትላለች እሷ፡፡ እሱ ደግሞ ምግብ ከተበላ በኋላ መዝናናት ነው እንጂ ምን አለፋሽ ቢላትም ስለማትሰማው እሷ ወደ ክሽና ስትሄድ እሱ ቴለቪዥን ከፍቶ እግር ኳሱን ይከሰክሳል፡፡
ሳሎኑና ክሽናው የተያያዘና ክፍት ስለሆነ ልጅቷ ከሱ አይን አትጠፋም፡፡ ታዲያ አንድ ጊዜ እግር ኳስ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ እሷን ከኋላዋ እያየ ጨርሳ እስከምትመጣ ድረስ መጠበቁን ከለመደ ሰንብቷል፡፡ አሁን ይቺ ልጅ ልክ እንደኔ በልታ ብታርፍ ምናለበት እያለ በማሰብ ያዝንላታል? አይኔንም ሁለት ቦታ ላይ ባታንከራትተው እያለ ያስባል፡፡

እሷም ስታጥብ አልፎ አልፎ ድንገት ብርጭቆ ይሰበርባታል፡፡ ብርጭቆ ሲሰበርባትም ምን አባቱ ማለት ታዘወትራለች፡፡ እሱም ይቺ ልጅ ብርጭቆ መሳደብ ትወዳለች እያለ በሆዱ ዝም ብሎ ሰነበተ፡፡ ይኸ ብርጭቆ መስበርና መሳደብ እየበዛ ሲመጣ አንድ ቀን እሱ እንዲህ አላት፡፡

እሱ፤ እንደቀልድ አድርጎ "አረ አንቺ ልጅ ምን አባቱ እያልሽ ብርጭቆ ሰብረሽ ልትጨርሺ ነው?"፡፡
እሷ፤ ዘወር አለችና "እጅሽን ስባሪው ቆረጠሽ ወይ እንደማለት? አንተ ለብርጭቆ ነው እምታስበው! እኔ ዝም ብዬ እለፋለሁ እንጂ አንተኮ ምንም አይገባህም፡፡ እዚህ አካባቢ ስመጣ እንዳትናገረኝ!" አለችው እራሷን እየነቀነቀች፡፡
እሱ፤ ዝም! ምክንያቱም አንድ ስለ ሴቶች አውቃለሁ ባይ ጥራዝ ነጠቅ ጓዴኛው እንዲህ ብሎ መክሮታል፡፡ "አየህ፤ ሴቶች ቁም ነገር ይሁንም አይሁን ተናግረው እንዲወጣላቸው ይፈልጋሉ፡፡ አንተ ብቻ አፍህን ዘግተህ አዳምጣቸው፡፡ ያኔ የተደመጡ ስለሚመስላቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ ቆጣ ቆጣ ማለት ሲጀምራቸው ደግሞ እዛው አካባቢ ቆይ እንጂ ነገር አበርዳለሁ ብለህ ከቤት ከወጣህ መመለሻ የለህም" ብሎ ስለመከረው ዝም ብሎ እንደተለመደው እግር ኳሱን ማየት መረጠ፡፡

ልጅቷም ተሳካላትና ብርጭቆ ሳትሰብር ብዙ ሰነበተች፡፡ እሱም እንዳለችው እዛ አካባቢ ስትሄድ አልተናገራትም፡፡ አንድ ቀን ታዲያ አጥባ ጨርሳ ወደሱ ስትመጣ ጸሃይ ስትወጣ የሚመስለውን ፈገግታዋን እያሳየችው ...
እሷ፤ "ሰሞኑን ምነው ጸጥ አልክ?" ብላ ጠየቀችው፡፡
እሱ፤ የዝምታ ዋጋ ይኸ ነው እንዴ እያለ በልቡ እያሰበ..... "እዛ አካባቢ ስደርስ እንዳትናገረኝ አላልሽኝም?" ብሎ ጥያቄውን በጥያቄ መለሰላት፡፡
እሷ፤ "ታዲያ እንደዛ ነው? በቃ፤ ጸጥ? "
እሱ፤ "አይ አፌ ዝም ቢልም ከዓይኔ አልጠፋሽኝም"፡፡
እሷ፤ "ወይ ጉዴ! እስከ ዛሬ ድረስ ከኋላዬ እያየኸኝ ነበር?"
እሱ፤ ከኋላሽ እንደማይሽ ስለምታውቂ አደለ ብርጭቆ እየሰበርሽ ምናባቱ እምትይው፤ ውሸታም! እያለ በልቡ፡፡ "ታዲያ ዓይንህንም ጨፍን ልትይኝ ትፈልጊያለሽ? አይዞሽ ቆንጆ ከመሆንሽ በስተቀር ምንም ጉድ የለብሽም፡፡ ይልቅስ አሁን ነይ ከጎኔ ሁኝና የሞቀ እግር ኳስ ግጥሚያ አብረን እንይ" ሲላት፤
እሷ፤ "ሂድ፡፡ ነገረኛ፡፡" ብላ ትታው ወደ ጓዳ ገባች፡፡
እሱ፤ አዬ እግር ኳስ፡፡ ጉድ ሰራኝ፡፡ አሁን እግር ኳስ ባይኖር ኖሮ ተከትያት ወደ ጓዳ እገባ ነበር እያለ በልቡ፡፡

Comments

የነገሩ ፈሊጥ በደንብ ገብቶኛል ፡ግን አልሳኩም ፡፡ለመሆኑ ጓዳ በአገራችን ዕቃ ቤት አይደለምን ??ከተሳሳትኩ ይቅርታ፡፡፡

እንዲህ በአገሬ ቋዋንቋ የማነብበትና የምፅፍበት መድረክ በማኖርህ ሁሌም አመሰግንሃለው፡፡

በርታ ታታሪው፡ለወገንህ ለቀሪው

ሌላውማ ሲያወራ፡ከአውሮፓ እስከ ደራ

የሚመስለው ሥራ ፡ በፉገራ

ይህው ታታሪው መጣ እያቅራራ፡፡

አክባሪህ ዳዊት መኮንን

ከልቤ አመሰግናለሁ!

ለገንቢ አስተያየትህ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ የጓዳ ስምን በተመለከተ ያው ልብስ መስቀያ ሳጥንና አልጋ የመሳሰሉት እቃ ከተባሉ ቦታውም አንዳኛ ስሙ ባይሆንም ጓዳ እንደሚባል ተስፋ አለኝ፡፡ በሃሳብህ ግን እስማማለሁ ዳዊት፡፡ ስታነብ ባለመሳቅህ ቅር ቢለኝም ምናልባት በኋላ ትስቅ ይሆናል፡፡ ይህንን ደግሞ ያስቃል ብሎ ነው እንዴ የጻፈው ብለህ? አንዳን ሳቆችኮ እንደዛ ናቸው? //ፋንታው

ሰላም!

ላስተያየትዎና ተጨማሪ በመፈለግዎ አመሰግናለሁ፡፡ ሆኖም ይች አጭር ጽሁፍ የምትቀጥል አይመስለኝም፡፡ //ፋንታው

HI tatariw

I have read your script .I love the way you write things . But i am afraid to say that your are more formal and very conservative in your writings , that makes it quite boring . You have used old styles of expressing things like professor Mesfin Woldmemariam . These days there are a lot of things to worry about and to be serious on , that is why many recent authors have tried to write dowm humoristic things more in informal languages. I can see that there are a lot of intersting things in your writings . Ya the only problem is your writing is quite hard and life-less. Have you experienced girls who have everything ;beautiful hair,structured face and everythings but not attractive . That expresses best your literature. SO work hard on mixing spices ..Like SHIRO ..BERBERE …Generally I apprciate your contribution . Keep on moving with making such corrections .

Debteraw

ለመልስና ላስተያየትዎ አመሰግናለሁ፡፡

እኔ አገላለጼ የሚደብር መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ እውነቴን ነው፤ የምጠቀምበት ቋንቋም አዲስ ይሁን የቆየ አላውቅም፡፡ እስኪ እንዲጥም ለመስራት እሞክራለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜም ስለ የተለያዩ ነገሮች ለመጻፍ አስቤ እንጂ ብዙወቹ ስራዎቼ ላይ ከምሬ ነው፡፡ ምናልባት እርስዎ አላነበቧቼው ይሆናል? //ፋንታው

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ