
ኮምፒውተር ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ ሰነድ ለመጻፍ፣ ሂሳብ ለማሰል፣ ኢንተርኔት ለመቅዘፍ፣ ለመጫወት፣ ለመሳል፣ ፎቶና ቪዴወ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም ኮምፕዩተር በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ ኮምፕዩተር እንዲሆንና ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡
አንደኛው የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HD ካዝና፣ RAM ራም ወይም ጊዜያዊ ተሸካሚ፣ Motherboard ዋና ካርድ፣ Sound card የድምጽ ካርድ፣ Video card የቪዴወ ካርድ፣ CPU አማካይ አዛዥ ይገኙበታል፡፡ እና የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ Display ማሳያ፣ Keyboard መጻፊያ፣ CD/DVD-rom የሲዲ/ዲቪዲ ቤት፣ printer ማተሚያ፣ Mouse አይጥ፣ ይገኙበታል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡
ሁለተኛው ክፍል ደግሞ አካላዊ ያልሆኑ ፕሮግራም ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ ሰነድ መጻፊያወች፣ ሂሳብ ማስሊያወች፣ ኢንተርኔት መቅዘፊያወች፣ ጨዋታወች፣ ስእል መሳሊያወች፣ ፎቶና ቪዴወ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም software ወይም የትእዛዝ ጥርቅሞች ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ ሃርድዌር የሚነካና የሚጨበጥ አይደለም፡፡ ሶፍትዌር ግን የባይነካና የማይጨበጥ ቢሆንም ክስተት የሚያሳይ የትእዛዝ ጥርቅም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የኮምፕዩተር የእያንዳንዱ የውስጥና የምጭ አካሎች የራሳቸው ድራይቨር (አስማሚ) የሚባል ሶፍትዌር አላቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ካርዱ የድምጽ ካርድ መሆኑን ኮምፕዩተሩ ውስጥ እንዲታወቅ ለማድረግ ነው፡፡
ሶስተኛው ክፍል ደግሞ Operating System ግብረተ ሲስትም ይባላል፡፡ የግብረተ ሲስተሙ ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ብዙ ሰወች ግብረተ ሲስተሙንና ሁለተኛው ነጥብ ላይ የተጠቀሰውን ሶፍትዌር አደባልቀውና አደናግረው ይነጋራሉ፡፡ ግን በቀጥታ ትክክል አይደለም፡፡ ባጭሩ ዋናው የግብረተ ሲስተሙ ስራ ግን የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ Windows ዊንዶውስ፣ Mac ማክ፣ Linux ሊነክስ የመሳሰሉት ግብረተ ስይስተም ናቸው፡፡
ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሉች ማለትም አካላዊ ክፍሎቹ፣ ፕሮግራሞቹና ግብረተ ሲስተሙ በአንድ ላይ ተቀናጅተውና ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡ እነዚህ ሶስቱም ክፍሎች እንዴት እንደሚሰሩ ሰሞኑን በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 45292 reads
Comments
በጣም ደስ የሚል ትምህርትና ቅንነትን በሰላም
በጣም ደስ የሚል ትምህርትና ቅንነትን በሰላም የሚታይበት ድህረገፅ ነው ታታሪው በጣም ወድጀዋለሁ አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ ቤተልሔም!
አመሰግናለሁ ቤተልሔም!
አሪፍ ነው ግን ኮምፒውተር ስንገዛ ማየት
አሪፍ ነው ግን ኮምፒውተር ስንገዛ ማየት ያለብን ዋና ዋና ነገሮችን ብትዘረዝርልን
ለምሳሌ ጉግለ ላይ Guide to buying
ለምሳሌ ጉግለ ላይ Guide to buying new pc ብሎ በመፈለግ የተሻለ አማራጭ ይገኛል፡፡ መልካም እድል!
good
good
የኮምፕዩተር ውስንነት ምንድነው?
የኮምፕዩተር ውስንነት ምንድነው?
ሰላም!
ሰላም!
የኮምፕዩተር ውስንነት በሰው ፕሮግራም ተደርጎ ካልተወቀረ በስተቀር በራሱ አይሰራም።
በጣም ጥሩ ነው 5-8ክፍል በቀሚነት እንዲሰጥ
በጣም ጥሩ ነው 5-8ክፍል በቀሚነት እንዲሰጥ ለሚመለከተው አካል ጣሩ
በጣም ደስ ይላል ሰፋ ያሉ የኮመፒውተር
በጣም ደስ ይላል ሰፋ ያሉ የኮመፒውተር ማንዋችን ብታዘጋጁ ሃሪፍ ነው
በጣም ጥሩ ትምህርት ነው
በጣም ጥሩ ትምህርት ነው
Pages
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ