You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የኮምፕዩተር አካሎችና የስራ ድርሻቸው፤ ክፍል ሁለት፡፡

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Tue, 01/07/2014 - 19:37
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic

ሶስት ቀን በፊት ኮምፕዩተር ምን እንደሆነና በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚከፈል አቅርቤ ነበር፡፡ በተጨማሪም እንዚህ ሶስት ክፍሎች ምን እንደሆኑና ስማቸውም ተጠቅሶ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ እንደት እንደሚሰሩ በዝርዝር ይቀርባል፡፡ ይህንን ሁለተኛውን ክፍል በሚገባ ለመረዳት የመጀመሪያውን ክፍል ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ስማቸውንና የስራ ድርሻቸውን ለማወቅ ከግራ በኩል ያለውን ስዕል እያዩ ማመሳከር ይቻላል፡፡

ዋና ካርድ Motherboard፡፡ ለመረዳት እንዲቀል ዋና ካርዱን በመጀመሪያ አብራራለሁ፡፡ ዋና ካርዱ የኮምፕዩተር ዋና/መሰረታዊ የአካል ክፍል ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም የውስጥም ይሁን የውጭ የኮምፕዩተር ክፍል ዋናው ካርድ ላይ ስለሚሰኩ ነው፡፡ ዋናው ካርዱ የተለያዩ የኮምፕዩተር አካሎች እርስ በርሳቸው እንዲገናኙና ተባብረው እንዲሰሩ የመገናኛ መንገድ ወይም ሃዲድ አለው፡፡

አማካይ አዛዥ Central Processing Unit፡፡ አማካይ አዛዡ የኮምፕዩተሩ አዕምሮ ነው፡፡ አማካይ አዛጁ ከሃርድዌርና ከሶፍትዌር የሚመጡትን ትእዛዞች ለማስተናገድ ሃላፊነት አለበት፡፡ በአንድ ሰከንድ ውስጥ በሚልዮን የሚቆጠሩ ትእዛዞችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ አማካይ አዛዡ የተለያዩ ትእዛዞችን በፍጥነት ስለሚያተናግድና ስራ ስለሚበዛበት በጣም ይሞቃል፡፡ ስለዚህ እራሱን የቻለ ማራገቢያ ካናቱ ላይ አለው፡፡
ትእዛዙንም ለማስተላለፍ ዋናው ካርዱ ላይ በብዙ እግሮቹ ተሰክቶ ይቀመጣል፡፡ አማካይ አዛዡ ከሌሎች አካሎች በበለጠ እጅግ በጣም ውስብስብ በሆነ ቴክኖሎጂ የተሰራ ነው፡፡
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic
የሲዲ/ዲቪዲ ቤት CD/DVD-rom፡፡ የሲዲ/ዲቪዲ ቤት እንደሚታወቀው ሲዲ/ዲቪዲ ላይ ሙዚቃ/ቪደወ/ፎቶ/ሶፍትዌር (ዴታ) የመሳሰሉትን ለማንበብ ነው፡፡ ወይም ዴታወቹን ሲዲ/ዲቪዲ ላይ ለማቃጠል ነው፡፡ የሲዲ/ዲቪዲ ቤቱ ከዋናው ካርድ ጋር እንዲገናኝ እንዲሁም ትእዛዝ እንዲቀበልና እንዲልክ በብዙ ሽቦወች ከዋና ካርዱ ጋር ይያያዛል፡፡

ካዝና Hard drive HD፡፡ ካዝና ዴታወችን በቋሚነት ቆጥቦ ለመያዝ ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ ሰነድ ጽፈው መቆጠብ ከፈለጉ የሚቆጠበው ካዝና ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው ካዝናው ዋና ካርዱ ላይ የሰካል፡፡ ካዝናው ዴታ ሲያነብና ሲጽፍ ማግኔታዊ ነው፡፡ የውስጥም ሆነ የውጭ ካዝና አለ፡፡ የዚህ አይነት ካዝና ከፍተኛ ንቅናቄ አይወድም፡፡ ለምሳሌ ኮምፕዩተርወ ከጠረንጴዛ ላይ ከወደቀ እንዳወዳደቁ ቢሆንም ካዝናው ሊበላሽ ይችላል፡፡ ባሁኑ ጊዜ ግን (2104 ) ፍላሽ የሚባሉ ግን ውድ የሆኑና በቀላሉ የማይበላሹ ካዝናወች አሉ፡፡

ራም Random Access Memory RAM፡፡ ራም የሚጠቅመው የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ ፕሮግራሞች በፍጥነት እንዲነዱ የሚጠቅም ነው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ኮፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ ከካዝና ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል፡፡ ፎቶ ወይም ቪደወ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና የቪደወ ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች እስከተከፈቱ ድረስ ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር የኮምፕዩተሩም ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ካርዱ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

ሃይል አዳይ Power Supply PS የሃይል አዳዩ ስራ የኤሌክትሪክ ሃይልን መጥኖ ለተለያዩ የአካል ክፍሎች ማደል ነው፡፡ ሁሉም የኮምፕዩተር አካል ክፍሎች አንድ አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል (ቮልት) አይጠቀሙም፡፡ ስለዚህ የሃይል አዳዩ ቮልቱን መጥኖ ለሁሉም ክፍሎች ይመግባል፡፡ ለምሳሌ 12 ቮልት፣ 9 ቮልት፣ 6 ቮልት፣ 48ቮልት ሊሆን ይችላል፡፡ ሃይል አዳዩ እራሱን የቻለ ማራገቢያ አለው፡፡

የድምጽ ካርድ sound board፡፡ የድምጽ ካርድ ኮምፕዩተሩ ድምጽ እንዲያመርት የሚያስችል ነው፡፡ ድምጽ ካርዱ ድምጽ ማውጫ ላይ የድምጽ ማጉያ በሽቦ ማያያዝ ይቻላል፡፡ የድምጽ ማጉያና ካርዱ ጥራቱ በጨመረ ቁጥር የተሻለ ድምጽ ያሰማል፡፡

ቪደወ ካርድ video card፡፡ ማሳያው/Display ላይ የሚታየው በሙሉ ቪደወ ካርዱ የሚያሳየውን ነው፡፡ ለምሳሌ የሚያነቡና የሚጽፉ ከሆነ ፊደወ ካርዱ እንዲታይ ያደርጋል፡፡ ፎቶና ቪደወም የሚያዩ ከሆነ ቪደወ ካርዱ ማሳያው ላይ ያሳያል፡፡ ተጠቀሚው የሚያያቸውና የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ እንዲታዩ የሚያደርገው ቪደወ ካርዱ ነው፡፡

የመጨረሻውና ሶስተኛው ክፍል በሚቀጥሉት ቀኖች ውስጥ ይቀርባል፡፡ ኦፐሬቲንግ ሲስተምና ፕሮግራሞች ምን እንደሆኑና እንዴት እንደሚሰሩ ይቀርባል፡፡

Comments

ሰላም!
የመጀመሪያው ክፍል፤ http://mejemeriya.com/basic-computer-knowledge-part1

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ