
የስራ ማመልከቻ የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ማመልካቻው ሲጻፍ ተገቢ ጥንቃቄና ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ ኮተትም ሳይበዛበት አጠር ብሎ ግልፅና ለመረዳትም ቀላል መሆን አለበት፡፡ ቀጣሪዎችም ብዙ ማመልከቻዎች ስለሚደርሷቸው እጥር ምጥን ያሉ ማመልከቻዎችን ይመርጣሉ፡፡ እንግዲህ ማመልከቻ ሲፅፉ ቀን፣ የእርስዎ ሙሉ ስምና አድራሻ ይቀድማል፡፡ ከዚያም የስራው አይነት ከነ አርእስቱ ጎላ ብሎ በአርእስት መልክ ገባ ብሎ ይሰፍራል፡፡ ወደ ዝርዝር ከመግባትዎ በፊት ስራውን በተመለከተ መቼና ከማን ጋር በስልክ ጥሩ ውይይት እንደነበረዎት ቢጠቅሱ ይታዎሳሉ፡፡ ከዚያም ይህንን ስራ ለምንና እንዴት እንደፈለጉት ባጭሩና በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡ የትምህርት ጊዜ፣ የስራ ልምድ፣ በትርፍ ጊዜወ የሚደረጉት የተለያዩ ዝንባሌዎች፣ ወዘተ እራሱን በቻለ ገጽ ላይ እጥር ምጥን አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡
በተጨማሪም አመልካቹ ባሁኑ ጊዜ ምን እንደሚያደርግና ህይወቱም ምን እንደሚመስል ቀንጨብ አድርጎ ቢያቀርብ ማመልከቻውን ሁለገብ ያደርገዋል፡፡ አመልካቹ በራሱ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የራሱን ሁኔታዎችና ልዮ ችሎታዎች ቢጠቅስ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመጨረሻም እርስዎን የሚያዉቁዎትንና የጠየቋቸውን የሁለት ወይም ሶስት ተጠሪ ግለሰቦች ስም ከነሙያቸው ያሰፍራሉ፡፡ ተጠሪዎቹም ድንገት ተደውሎላቸው እንዳይደናገሩ ጉዳዩን በቅድሚያ ይንገሯቸው፤ ያስታውሷቸውም፡፡ ማመልከቻውም ከተላከ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት በኋላ ከዚህ በፊት ያነጋገሩት ሰው ዘንድ መደወል ጥሩ ነው፡፡ ስልኩንም እራሱ ሰውዬው ካነሳው/ችው በስም ሰላም እከሌ ብሎ ንግግር መጀመር ነው፡፡ ለምሳሌ በዚህ ቀን ላይ ስለዚህ ስራ ተነጋግረን ነበር፡፡ ማመልከቻ ልኬአለሁ፡፡ ስለ ማመልከቻው ምን ይመስልዎታል? ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልጉት ካለ መላክ እሽላለሁ ብሎ መጠየቅ ይጠቅማል፡፡ ማመልከቻው እስከዛሬ ድረስ ያልተነበበ ከሆነ አርስዎ ስለደወሉ ማመልከቻው ከተቀመጠበት ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊነበብ ይችላል።
ዋናው ቁም ነገር ግን አርስዎ አሁን እራስዎን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አስተዋወቁ፡፡ የራስዎንም ማመልከቻ በደንብ ተከታተሉ፡፡ ከዚህ በፊት ያነጋገሩትንም ሰው በስም አስታወሱ፡፡ ይህንንም ስራ ለማግኘት ፍላጎትዎን እንደገና አሳዩ፡፡ ማመልካቻውም ከንብብሩ ላይ ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊታይልወት ይችላል፡፡ ቀጣሪውም አርስዎን በቀላሉ ያስታውሰዎታል፡፡
ንግግሩም በሚካሄድበት ጊዜ እርስዎ እንደ ስራ ለማኝ ወይም ተስፋ ቢስ አይነት ሆነው መቅረብ የለብዎትም፡፡ ባነጋገር ሁኔታና በድምፅ ቃና በራስዎ የሚተማመኑ መሆንዎን ማሳወቅ መቻል አለብዎት፡፡ ይህ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሳይጠበቁ ድንገት ለሚመጡ ጥያቄዎችና መልሶች በስልክም ቢሆን ቅሉ ዝግጁ መሆንና በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ጥያቄ ማቅረብና መልስም መስጠት ከቀጣሪው ዘንድ ነጥብ ያሰጣል፡፡ መጨረሻም ላይም አመስግኖ ለቃለ ምልልስ እንድምጠራ ተስፋ አደርጋለሁ ሳይሆን ለቃለ ምልልስ እንደምጠራ እጠብቃለሁ ብለው በጨዋነት የስልኩን ንግግር መደምደም ነው፡፡ ዘንድሮ እኮ በጣም ፈጣጣና አይን አውጣ ሆንኩኝ ብለው አይስጉ።
ዋናው ነገር ወሬ ሳያበዙ ባጭሩ መጠየቅ፣ መልስ መስጠትና በጊዜው ውይይትዎን መጨረስ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ለቃለ ምልልስ ካልተጠሩ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ሌላ ስራ ለማግኘት ስራ ማደንወን መቀጠል ነው፡፡ ለቃለ ምልልስ ከተጠሩ ደግሞ እሰየው ነው፡፡ አንድ እርምጃ ወደፊት፡፡
ለማስታወስ ያህል እስካሁን ድረስ የሚከተሉትን ነጥቦች በዝርዝር አይተናል፤
1. ለስራ ፍለጋ ቅድሚያ ዝግጅት፣
2. ክፍት የስራ ቦታዎች ምን ላይና እንዴት እንደሚወጡ፣
3. ማመልካቻ ከመጻፉ በፊት ስለሚደርጉ ቅድመ ዝግጂቶችና፣
4. የማመልከቻ አጻጻፍና ክትትሉን አይተናል፡፡
አሁን ደግሞ ለቃለ-ምልልስ ከተጠሩ ስራውን ለማግኘት ምን መደረግ እንዳለበት በሚቀጥለው ክፍል ላይ በዝርዝር እናያለን፡፡
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 29401 reads
Comments
ሰላም ታታሪው
ሰላም ታታሪው
የግብር ቅሬታ ማመልከቻ ፎረም ልትጽፍኝ ትችላለህ?
ሰላም!
ሰላም!
ይቅርታ! የግብር ቅሬታ ህጉን ስለማላውቅ ቅጹን መጻፍ አልችልም፡፡ እርስዎ የሚኖሩበት ሃገር ውስጥ እራሱን የቻለ ተሰርቶ ያለቀ የቅሬታ ቅጽ ይኖራል ብየ እገምታለሁ፡፡ ምናልባት ኢንቴርኔት መስመር ላይ ወይም ቢሮ ሄደው ወረቀት ላይ ሊገኝ ይችላል፡፡ መልካም እድል፡፡ //ፋንታው
God bless you for all hard
God bless you for all hard work you put on this website. I'm sorry I don't know how to use the Amharic key board. I have been looking this kind of website to teach my husband who does not speak Amharic. "Amlake Egegg adrego yebarkhe" I like your humbleness and your way of trying to help our sisters and brothers around the world. I just run to your website by accident and liked all the work you do!!
መጀመሪያ ዶት ኮም ላይ የተሳፈውን ስለወደዱት
መጀመሪያ ዶት ኮም ላይ የተጻፈውን ስለወደዱት አመሰግናለሁ አዜብ! እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ሰው የተቻለውን መልካም ነገር ካደረገ ለመሻሻል መንገድ ይከፈታል፡፡ መልካም ቀን/ምሽት! //ፋንታው
የስራልምድ አጻጻፍ ፎርም እንዴት እንደሆነ
የስራልምድ አጻጻፍ ፎርም እንዴት እንደሆነ ብትልክልን
ይቅርታ እራሴ የሰራሁት ቅጽ የለኝም፡፡ ሆኖም
ይቅርታ እራሴ የሰራሁት ቅጽ የለኝም፡፡ ሆኖም ግን ምናልባት job seeking form ወይም ተመሳሳይ ቁልፍ ቃል ጉግለ ላይ አስገብተው ከበረበሩ መረጃና ቅጽ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ መልካም እድል!!
ሲኦሲ ለመፈተን አዳዲስ መረጃ ካለህ እስኪ
ሲኦሲ ለመፈተን አዳዲስ መረጃ ካለህ እስኪ ብታግዘኝ!
ይቅርታ ስለ ሲኦሲ ብዙ አላውቅም። ኢንተርኔት
ይቅርታ ስለ ሲኦሲ ብዙ አላውቅም። ኢንተርኔት ላይ ፈልጌ የሚያምታታ የተለያዩ መረጃወች ባገኝም የትኛው እንደሚሻል ማወቅ ያስቸግራል። አማዞን ላይም አግኝቼ ነበር ግን የሚፈለገው ለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም። ምናልባት ትንሽ በዝርዝር ከነገሩኝ መተባበር እችላለሁ።
የሰርግ የጥሬ ወረቀት እንደት ነው ማዘጋጀት
የሰርግ የጥሬ ወረቀት እንደት ነው ማዘጋጀት የሚቻለው
በመቀጠል ላሳወቃችሁን ነገር ከልብ እናመሰግናለን
ለምሳሌ ማክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ለመጀመር የሚሆን
ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ለመጀመር የሚሆን ምንጣፍ አለ። ወይም ኢንተርኔት ላይ wedding invitation templates ብሎ መፈለግ ይቻላል። መልካም እድል!
Pages
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ