You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ቁርስ የመብላት ጥቅምና አስፈላጊነቱ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sat, 02/21/2015 - 11:06

ልጅነቴ ጀምሮ ቁርስ በደንብ መብላት ሰውነትን ደግፎ ይውላል ሲባልና ቤተሰብ ውስጥም ሲነገር እንደነበር አስታውሳለሁ። ሰውነትን ደግፎ ይውላል ማለት በዝርዝር ለምን እንደሆነ በሳይንስ ማስረጃ ባይደገፍም በልምድና በሙከራ ግን የተደገፈ ነበር። ሳይንስ የሚሰራው በልምምድና በሙከራ ስለሆነ "ቁርስ ሰውነትን ደግፎ ይውላል" የሚለው አባባል ቁርስ ጥርግ አርጎ መብላት ይጠቅማል ለማለት ይመስላል። ። ቁርስ ከምሳና ከራት የበለጠ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ከእንቅልፍ በኋላ ጧት ስንነሳ ሆዳችን ምግብ አጠቃላይ ሰውነታችን ደግሞ ሃይል ስለሚያስፈልገው ሳይንስና ማስብ ብዙም አያሻው። በራሱ ግልጽ ነው። ከእምነትና ከጾም ጋር ካልተያያዘ በስተቀር ቁርስ በደንብ መብላት ብዙ ጥቅም አለው። ለምሳሌ የሃሳብም ሆነ የአካል እንቅስቃሴ ሃይል ለማግኘት፣ የበለጠ በረጅሙ ጤናማ ለመሆንና ንቁ ለመሆንም ይረዳል።

የቁርስ አይነትን በተመለከተ ግን ጤናማ ቁርስ መሆን አለበት። ጤናማ ቁርስ ምን እንደሚያቅፍ የእያንዳንዱ ሰው ምርጫና አቅም ስለሆነ የተወሰነ ቁርስ ስም ይኸ ነው ብዬ መጥቀስ የቁርስ ምግብ አይነቶችን መጥቀስ አልችልም። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ለአብዣኛው ህዝብ ሊያስቸግር ይችላል።

ጥቂት ብቻ ቁርስ የሚበሉ ወይም ከነጭራሹ ቁርስ የማይበሉ የማውቃቸው ሰወች አሉ። ቁርስ ለመብላትም የሚቸገሩ ሰወች እንዳሉም እሰማለሁ። ጧት ወደ ስራ፣ ት/ቤት ወዘተ ቶሎ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ጊዜ ለመቆጠብም ሲሉ ቁርስ ሳይበሉ የሚወጡም አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ በጣም በተለየ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ሰው ቁርስ በልቶ መውጣት ይችላል ይመስለኛል። ምናልባት ሁለቱ ዋናወቹ የችግሩ መንስኤዎች ቁርስ ለመብላት ጊዜ ማነስና የፍላጎት ማነስ ናቸው።

ዜን በተመለከተ ለቁርስ ቢያንስ አንድ ሰእዓት ወይም ከዛ በላይ መጠቀም ከጊዜ ጋር የተያያዘ ራስ የፈጠረውን ወከባ መቀነስ ይቻላል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ከእንቅልፍ ቀደም ብሎ መነሳት አንዱ ምርጫ ነው። በመጀመሪያ ወዲያውኑ እንደተነሱ አጭር ጸሎት ማድረግ። ከዛም ለምሳሌ 15 ዲቂቃወች ለመታጠቢያ፣ ቢያንስ 35 ደቂቃወች ቁርስ ለመብያ ከዛም መጨረሻ ላይ 15 ደቂቃ ጥርስ መቦራሻና መውጫ ጊዜ ሊሆን ይችላል። ቤተሰብና ልጆች ሲኖሩ ደግሞ እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋል። ትንሽ ጊዜ ለመቆጠብና ጭንቀት ለመቀነስ ደግሞ ማታ ላይ ምን አይነት ቁርስ ጧት እንደሚቀርብ ማቀድ ወይም ማወቅ ይቻላል። ጊዜ መጠቀሙ ለመረጋጋትና ቁርስም ግጥም አድሮ በልቶ ጥሩ መንፈስ ላይ ሆኖ ለመውጣት ይረዳል። እንዳውም ከመውጣት በፊት ለ2 ደቂቃወች ያህል አጭር ጸሎት አድርጎ መውጣት ብሩህና ጥሩ መንፈስ ያላብሳል ብዬ አምናለሁ። መጨረሻ ላይም ከቤት የመውጫ ጸሎት አንድ ዐረፍተ ነገርም ልትሆን ትችላለች። ለምሳሌ "አምላኬ አዕምሮዬን ብሩህ፤ ልቤን ደግሞ ደግ አርግልኝ" ብሎ ውልቅ ብሎ መውጣትም ይቻላል።

ቁርስ ፍላጎትን በተመለከተ ሰወች የተለያየ ምክንያት ቢኖረቸውም ዋናው ምክንያት ግን ከአስተሳሰብና ከጭንቅላት ጋር የተያያዘ ይመስለኛል። ለምሳሌ በቃ እኔ ቁርስ አይበላልኝም ብሎ መቁረጥ አንዱ ትልቁ እንቅፋት ነው። ቁርስ የመብላት ፍላጎትን ለማሻሻል ሦስት ምክንያቶችን መጠቀም ይቻላል። ሁለቱ ከላይ እንደጠቀስኩት ቁርስ የመብላት ጠቀሜታውንና ጊዜም መጠቀም እንደሚያስፈልገው ማስታወስ ናቸው። ሁለቱን ነጥቦች ሰው ካስታወሰ ፍላጎቱ ሊጨምር ይችላል። ቁርስ በልቼና ነቃ ብዬ መውጣት አለብኝ ብሎ ማሰብም ይረዳል። ሦስተኛው ደግሞ የቁርሱ አይነት ነው። ለምሳሌ ቁርስ ድርቅ ያለ ሲሆን ሊደብር ይችላል። በማላመጥ ጊዜ ይወስዳል። ለመዋጥም ትንሽ ያስቸግራል። ይህንን ችግር ለመፍታት ረጠብና ለስለስ ያለ ቁርስ ማዘጋጀት ቁርስ የመብላትን ፍላጎት ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

በኛ በኢትዮጵያውያን ባህል ጥሩ የቁርስ ባህል ያለን ይመስለኛል። የፍርፍሩ አይነትም ብዙ ነው። ሆኖም ግን ምናልባት ቅባት ባይበዛበትና ቁርስ በደንብ የሚበላው ሰው ያለው ቢሆንም ሁሉም እንደ አቅሙ ቁርስ በደንብ የመብላትና የመምረጥ አቅም እስካለው ድረስ ቁርስ ግጥምና ጥርግ አድርጎ መብላት ከምሳና ከራት ይበልጣል።

main category:

Comments

Yaw endalkew teru kurs meblst tenama new honom kekurs befit ye 20 dekika tselot yasfelgal yetselotun seat asaterkewa leje kursema eyehedum birom any plas can eat.yemeslegnal meches kes aydelehu ...mekereh gen arif new Fantaw berta.

ለአስተያየትዎና ለእርማትዎ አመሰግናለሁ አባ! የኔ ነገር የጧት ጸሎት ከሁሉም ነገር በፊት መሆኑን ለመጻፍ ሳትኩት። በየቀኑ ባይሆንም እኔም እራሴ ከሁሉም በፊት የማደርገው ነው። አሁን ጽሁፉን አስተካክያለሁ። በድጋሜ አመሰግናለሁ። //ፋተ

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ