You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

አላማና መነሻ ባጭሩ፤

ፋንታው ተሰማ ታታሪው መጀመሪያ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

ዲያስ!
እንኳን ወደ መጀመሪያ ዶት ኮም ልዩ ጣቢያ መጡ! የቀድሞው ታታሪው ዶት ኔት፡፡ ፋንታው ተሰማ እባላለሁ። ኖርዌይ ውስጥ የምኖር የኢትዮጵያ ልጅ ነኝ። ከኖርዌይም ሆነ በራሴ መንገድ ሰው በአቋሙ እንዴት ጠንካራ እንደሚሆን ልብ ብያለሁ። የመጀመሪያ ጣቢያ ዋና አላማ ኢትዮጵያውያን ቆንጆ አስተሳሰብና ጠንካራ አቋም እንዴት ማዳበር እንደሚችሉ መንገድ ለማሳየት ነው። ከኔ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ግን ዘንግቼ አይደለም።

ቆንጆ አስተሳሰብ ስል አዕምሮአችን ሚዛናዊና ምክንያታዊ ሆኖ ቅን ሰው መሆን እንድንችል ለማሳየት ነው። ሰው አስተሳሰቡ ቆንጆ ከሆነ በሌሎች ይወደዳል። መቼም ሁሉም ሰው መወደድ ይፈልጋል!!

ጠንካራ አቋም ስል ደግሞ ለማሸነፍ ደፍሮ ውሳኔ መስጠትን መለማመድ እንደሚቻል ለማሳየት ነው። ድክመት፣ ዝምታና ስንፍና በድፍረትና በድል እንዲተኩ ማድረግ ይቻላል። ኢትዮጵያ ጠንካራ አቋም ያለው ደፋር ዜጋ በብዛት ካመረተች፤ ደረቷን ነፍታ፣ ትካሻዋን ከፍና አንገቷን ቀና አድርጋ ተከብራ መኖር ትችላለች። ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ይኮሩባታል። አክብረው ይጠብቋታል። ይወዷታል። ይንከባከቧታል። የሃገር ፍቅር ማለት ይኸ ነው።

እርግጥ አንዳንድ ወቀሳወች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በጥንቃቄ የተላበሰ ወቀሳ የማቀርበው ግን ደካማ በሆነ አስተሳሰባችን ላይ እንጂ ግለሰቦችን እንዳልሆነ ከወድሁ አሳስባለሁ፡፡ ለጨለማ ጊዜ መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለችገር ጊዜም ብልሃትና እውቀት ያስፈልጋል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን ህይወቱን ለማሻሻል ሁሉንም ነገር በራሱ ብቻ ማወቅ አይችልም። የሰው ልጅ በማንበብ፣ በመማር፣ በማየትና በማዳመጥ፣ ደጋግሞ በመለማመድ በብዙ ነገሮች ላይ አዋቂና ብልህ መሆን ይቻላል። ማንኛውም ነገር ትምህርት ያስፈልገዋል። ቆንጆ አቅጣጫ የሚያሳይና የሚያለማምድ ያስፈልገዋል። የራስ ትኩረት፣ ክትትልና መለማመድ ያስፈልገዋል። የጋራ ትብብር ያስፈልገዋል።

ሰው ልጅ፤ ብዙውን ጊዜ እውነቱ በአንድ ጊዜ ፍርጥ ብሎ ሲነገረው ላይወድ ይችላል፡፡ በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ አይነት ስህተት በመስራት አንደኛ ሳንሆን አንቀርም። ምክንያቱም ብዙ ኢትዮጵያያን በህይወታቸው ላይ የሚወስዱት አቋምና እርምጃ ትክክል ስለመሆኑ ለመጠራጠር በቂ ምክንያት ስላለ ነው። ጥቂት ነገሮች ላይ ትክክል ብናስብም ብዙ ስህተቶች እንሰራለን። ትክክሎች መብዛት ነበረባቸው። ስህተቶች ደግሞ በጣም ማነስ ነበረባቸው።

የሆነ ጊዜና ቦታ ላይ ግን የሆነ ሰው መናገር አለበት፡፡ እኔ መጀመሪያ ጣቢያ ላይ የምጽፈው ማንንም ለመቀየር አይደለም። ነገር ግን በጥልቅ አስበውና አመዛዝነው ቆንጆ አስተሳሰብና ጠንካራ አቋም ማደበር ከሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመግባባትና ለማገዝም ጭምር ነው። የኢትዮጵያ ወደኋላ መቅረት መንስኤው የቆንጆ አስተሳሰብና ጠንካራ አቋም እጦት ነው ብዬ አምናለሁ። የልብ ውህደትና የአዕምሮ አንድነት ማዳበር በጣም ያስፈልገናል። ብዙ ሰወች አንድነት ሃይል ነው ይላሉ። አንድነት ግን ብቻውን ሃይል አይሆንም። ምክንያቱም ሰወች ተስማምተው አንድነት ለመፍጠር መጀመሪያ በእውቀት መታነጽ አለባቸው።

ስለዚህ ሃይል ሊመጣ የሚችለው ሰወች ካወቁ በኋላ አንድ ለመሆን በጋራ ሲስማሙ ነው። ሰው ዝም ብሎ አንድነት ሃይል ነው ካለ መፈክር ብቻ ሆኖ ይቀራል። የመጀመሪያ አንዱ አላማ ይህንን ግልጽ ለማድረግ ነው። እርስ በርስ አይዞን እንዲንባባል ነው። ከግላችን አልፈን ወገን እና ሃገር የሚለውን ትልቁን ስዕል በሰፊው እንዲናይ ለማድረግ ነው። ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው መሆናችንንም ጭምር የሚፈታተን ሃሳብ ለማስተዋወቅ ነው። አሁን አይፍረዱብኝ፤ እዚህ ጣቢያ ላይ ካነበቡ በኋላ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የቱን ያህል ባጋጣሚ እንደሚኖር ይገለጥለዎታል።
tatariw ethiopia Amharic addis ababa
ይህ ፅሁፍ በትርፍ ጊዜዬ ከማደርጋቸውና ከሚያስደስቱኝ ዝንባሌዎወች አንዱ ነው፡፡ ሙያየ አይደለም፡፡ ነገር ግን "ሞኝ ውኃ ሲወስደው ይስቃል" እንደሚባለው ሆነን እንዳንቀር ለወገንና ለሃር በማሰብ ነው የምፅፈው፡፡ ይህ ማለት ችግር እያለብን እንደሌለብን ሆነን ባለንበት መቀጠል አያስፈልግም፡፡ ሰፊና ሁለገብ የሆነ ብልሃትና እውቀት ያስፈልገናል። በተረፈ ይህ ጣቢያ ዜና አይደለም። ነገር ግን የማውቀውን፣ የማምንበትንና ፈትኜ የሰራልኝን አቋም ለማካፈል ነው። እንዴት እንደሚሰራም በቀላሉ ለማስረዳት ነው። በተጨማሪ መጀመሪያ ላይ አሉባልታና ጥላቻ የለም። ስለዚህ ልብዎ ቢወድ ትርፉ መወደድ ነው። አስተሳሰብዎ ቢጠነክር ትርፉ መከበር ነው። ልብዎ ቢወድ ደካማና ፈሪ ሰው አይሆኑም። አስተሳሰብዎ ቢጠነክር መጥፎ ሰው አያደርገወትም። በመውደድና ጠንካራ በመሆን ግን ያሸንፋሉ። ይከበራሉ። በዚች አለም ውስጥ ሁሉንም ጥሩ ነገሮች የሚወስደው አሸናፊ ብቻ ነው። ታሪክም እንደሚያሳየን አሸናፊ ሰው የሚፈልገውን አጥቶ አያውቅም። ምክንያቱም ለማሸነፍ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። ትልቅ ነገር ባያደርግ እንኳን ቢያንስ ውስጡ በሰላምና ጥንካሬ የሞላ ይሆናል።

ሚስተካከሉት ነገሮች ብዙ ናቸው። ጊዜና ልምምድ ይፈልጋሉ።
አሁን ግን የሚከተሉትን ጥያቄወች ለምሳሌ፤

  • ጠቃሚ ነኝ ወይስ አይደለሁም?
  • በሥራ ሰነፍ ነኝ ወይስ ጎበዝ?
  • ክፉ ሰው ነኝ ወይስ ደግ ሰው?
  • ከራሴ አልፌ የተቸገረ መርዳት እችላለሁ?
  • ኢትዮጵያ ከኔ ምን ትጠብቃለች?
  • ነጻ ለመሆን መብትና ግዴታየን አውቃለሁ?
  • የማሰብ፣ የመስራትና የመውደድ አቅሜና ፍላጎቴ ከፍተኛ ነው?

.....ብለው ከጠየቁ እራስዎን እንዲመረምሩ መንገድ ይከፈትልወታል።
ጾታዎ ወንድ ሆነም ሴት፤ እድሜዎ አምስትም ይሁን ሰማንያ ትምህርት አያልቅም፡፡ ስለዚህ ይቺን ልዩ ጽሁፍ አንብበው ከወደዷት በተግባር እንዲተገብሯት በአክብሮት እጠይቀዎታለሁ፡፡ ለጓደኞችዎም ያስተዋውቁልኝ። ጥሩ ሃሳብ ማንነትን ሳይሆን ህይወትን ይቀይራል። ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ቢሆንም አማርኛ ማንበብ ለሚችሉ ሌሎች ሃገር ዜጎችም ጭምር ይጠቅማል፡፡

መጀመሪያ የትምህርት መስጫና የሞራል መገንቢያ ቦታ ነው፡፡ የሚብለጨለጭ ነገር እዚህ የለም፡፡ ስለዚህ ተረጋግተውና ሃሳብዎን አጠቃለው እንድያነቡ ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡ በተረፈ መልካም ምንባብ። አስተያየትዎም አይለየኝ! አመሰግናለሁ።
ባጠቃላይ በህይወትዎ ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያውቃሉ? እራስዎ!!!

ቅድስት ኢትዮጵያ ሃገራችን ለዘለአለም ትኑር!
ሁሉም ልጆቿ በአስተሳሰባቸው ቆንጆ እና በአቋማቸው ጠንካራ ይሁኑ!

ኢትዮጵያ ተነሺ!
ለውድቷ እናቴ ለወርቅነሽ ተሰማ መታሰቢያ ይሁን፡፡

መጀመሪያ ዶት ኮም

Comments

ሀይ ፋንታሁን
በጣም በጣም አድናቂህ ነኝ ለሀገርህ ግዝቦች ስብእና መጨነቅህ በራሱ ፍፁም ቅንና አፍቃሪ ልብ እንዳለህ ያመለክተል፡፡ግን አንዳንዴ የፖለቲካ የሚመስል የፖርቲ ስም እየጠቀስክ የምትፅፈው አልተመቸኝም ይሄ ብዙ ቦታ አለ ሰልችቶናል እሱን ስሜትህን ተወው በተረፈ ጎበዝ ሳይኮሎጂስት ነህ
እድሜና ጤና ይስጥህ በዚሁ ቀጥል ብዙ እንጠብቃለን

ሰላም!
ለአስተያየት፣ ትችትና ምርቃት አመሰግናለሁ። እዚህ ታታሪው ጣቢያ ላይ የፖለቲካ ነገር የሚመስል ተጋኖ የተጠቀሰ አይመስለኝም። ይህ በዚሁ እንዳለ እኛ ኢትዮያውያን ወደኋላ የቀረነው የአስተዳደር ችግር ስላለን ነው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ክፉውን ለመንቀፍና ደጉን ለመደገፍ የሚጠቀምበት መንገድ ጥራት የለውም። ስለዚህ እኔ ይህንን በተመለከተ በጣም ጥቂት ነገር ባነሳም የተሰማኝን መጻፍ መቻል አለብኝ። ሁሉም ነገር ነጭና ጥቁር መሆን ስለማይችል አስፈላጊ ቦታ ላይ መጥቀስ ያስፈልጋል ይመስለኛል። //ፋተ

Today we need 10's of thousands like you, You are the man of today who thinks about his country people and his homeland.
May God Bless You,

I am happy you found the idea on Tatariw useful. Thank you! There is a need for well-balanced character among many Ethiopians, and the sooner the better. //Fantaw

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ